COVID-19 (በፊት “ኖቬል ኮሮናቫይረስ” ተብሎ የሚታወቀዉ) የህዝብ ጤና ምክረ ሀሳቦች
COVID-19 Public Health Recommendations in Amharic
?COVID-19 ምንድነዉ
COVID-19 (በፊት “ኖቬል ኮሮናቫይረስ” ተብሎ የሚታወቀዉ) ከሰዉ ወደ ሰዉ እየተሰራጨ ያለ አዲስ ቫይረስ ነዉ። ምንጩ ከቻይና ሆኖ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካና ብዙ ሌሎች አገሮች ይገኛል።
እንዴት ነዉ ኖቬል ኮሮናቫይረስ (COVID-19) የሚሰራጨው?
የጤና ባለሙያዎች ስለስርጭቱ አሁንም ተጨማሪ እየተማሩ ነው። በአሁኑ ሰዓት ይሰራጫል ተብሎ የሚታሰበዉ፡
በበሽታዉ የተየዘ ሰዉ ስያስነጥስና ስያስል በትንፋሽ ጠብታዎች ዉስጥ
ቅርብ ለቅርብ በሆኑ ሰዎች መካካል (በ6 ጫማ ርቀት ዉስጥ)
ቫይረሱ ያለበት ነገር ከነኩ በኋላ አፍ አፍንጫ ወይንም ዐይን በመንካት
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
የኖቭል ኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ለቫይረሱ ከተጋለጡ በኋላ ቢያንስ በ2 ቀናት ውስጥ ወይም ቢበዛ እስከ 14 ቀናት ድረስ ምልክቶች ይታዩባቸዋል።
ለከፋ የ COVID-19 በሽታ በከፍተኛ የተጋላጭነት ስጋት ላለባቸዉ ሰዎች ምክር
የህዝብ ጤና ለከፋ ህመም ተጋላጭነት ስጋት ላለበቸው ሰዎች ቤት እንዲቀመጡና ብዙ ሰዎች ካሉበት ስፍራ በተቻለ መጠን እንዲርቁ ይመክራል። የከፋ ህመም ተጋላጭነት ስጋት ያለባቸው ሰዎች የሚጨምረዉ፡
ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ
ሌላ ቀደም ያለ የጤና ችግር ያለባቸው፤ የልብ ህመም፣ ሳምባ በሽታ ወይንም ስኳር ያለባቸውን ጨምሮ
በሽታ የመከላከል አቅማቸዉ ደካማ የሆኑ
እርጉዝ የሆኑ
ማንኛዉም የጤናቸው ሁኔታ ለከፋ COVID-19 ህመም ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸዉ ጥያቄ ካላቸው ከሃኪሞቹ ጋር መማከር አለባቸው።
ለትላልቅ ኩነቶች፣ ስብስባዎችና ድርጅቶች የወጣ መመሪያ
መጋቢት 16 2020 የማህበረሰብ ጤና የሚከተሉትን መግለጫዎች አውጧል፡
ከ50 ተሳታፊዎች በላይ የሚገኙበት ኩነቶች ተከልክሏል።
ከ50 በታች ተሳታፊዎች ለሚገኙባቸዉ ኩነቶች ስጋት ለመቀነስ የሚከተሉትን 5 እርምጃዎች መወሰድ አለባቸዉ፡
የታመሙ ፣ 60 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑትንና ቀደም ያለ የጤና እክል ያለባቸዉ ሰዎችን እንዳይሳተፉ መገፋፋት
ለሰዎች ብዙ ክፍተት ለመስጠት መንገድ መፈለግ በተቻለ መጠን ቅርብ ለቅርብ እንዳይሆኑ
የኩነት አዘጋጆችን፣ ሠራተኞችና ተሳታፊዎችን ምልክቶች እንዳለባቸዉ መለየት
ሰዎች እጃቸዉን በሳሙናና ዉሃ ወይንም ሳኒታይዘር መታጠብ መቻላቸዉን ማረጋገጥ
በየግዜው የምነኩ እቃዎችንና ላያቸዉን በየቀኑ ወይንም ከዚያ በላይ ያጽዱ
ሁሉም መጠጥ ቤቶች፣ የደንስ ክበቦች፣ የጤና ክበቦች፣ የፊልም ቲያትር ቤቶች፣ ምሽት ከበቦችና ሌሎች የማህበራዊና መዝናኛ ቦታዎች እስከ መጋቢት 31 2010 ድረስ ዝግ ይሆናሉ።
ሁሉም ሬስቶራንቶችና የምግብ አገልግሎት አቅራቢ ቦታዎች የመመገቢያ ክፍል አገልግሎት ያቆማሉ፤ ሆኖም ግን በተሽከርካሪ ገዝቶ ለማለፍ፣ ገዝቶ ይዞ ለመዉጣትና የማድረስ አገልግሎቶች እስከ መጋቢት 31 2010 ድረስ ክፍት ይሆናሉ።
ሌሎች የሽያጭ ቦታዎች ሁሉ እንደ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆች፣ መድሃኒት ቤቶች፣ ባንኮች፣ ነዳጅ ማደያዎች፣ ህንጻ መሣሪያ ሱቆች፣ ገበያ ማእከላት የመሳሰሉት ከላይ የተጠቀሱትን 5 እርምጃዎችን ሰጋት ለመቀነስ እስካሟሉ ድረስ ክፍት ይሆናሉ። የCOVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ለሽያጭ ድርጅቶችና አገልግሎት ሰጪዎች ምክርን የግድ መከተል አለባቸዉ።
ይህ ትእዛዝ የሚመለከተዉ የህዝብና የግል የሥራ ስብሰባዎች፣ ማህበራዊ ወይንም የመዝናኛ ተግባራትን፡ በነዚህ ብቻ ሳይወሰን፤የማህበረሰብ፣ የህዝብ መዝናኛ፣ ወይንም ስፖርታዊ ኩነቶች፣ ሰልፎች፣ ኮንሰርቶችና ዝግጅቶች፣ ፌስቲቫሎች፣ ትላልቅ ስብሰባዎች፣ የገንዘብ ማሰባሰቢያዎች፣ የሃይማኖት አገልግሎቶችና ተመሳሳይ ተግባራትን ይጨምራል።
በተጫማሪም የCOVID-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡
መጨባበጥ እንድያቆሙና ሌሎችን ሳይነካኩ ሰላም የሚባባሉበትን ዘዴዎች ይጠቀሙ።
በር ላይ እጆቻቸዉን ያጽዱ።
ክፍያ ለመፈጸም ስልካቸዉን ወይንም የማይነኩ ክሬድት ካርዶችን ይጠቀሙ ጥሬ ገንዘብ ጋር ንክኪ ለመገደብ።
ፊታቸዉን መንካት ለማስወገድና ስያስሉና ስያስነጥሱ ለመሸፈን አዳዲስ ልምዶችንና ማስታወሻዎችን መፍጠር።
ምክር ለሥራ ቦታዎች
በዚህ ወሳኝ የድንገተኛ ወቅት ከተቻለ ብዛት ያለቸዉን ሰዎች አንድ ላይ ማምጣትን ማስወገድ፣ ኩነቶችንና ስብስባዎችን ማስተላለፍ። ሰዎች አንድ ላይ ማምጣትን ማስወገድ የማይችሉ ከሆነ፤
የታመመ ሰዉ እንዳይሳተፍ መገፋፋት
ለ COVID-19 በከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑትን እንዳይሳተፉ ማበረታታት
ለሰዎች ብዙ ክፍተት ለመስጠት መንገድ መፈለግ በተቻለ መጠን ቅርብ ለቅርብ እንዳይሆኑ
ተሳታፊዎችን እንደ ቶሎ ቶሎ እጅ መታጠብ ያሉትን መልካም ልማዶችን እንዲቀጥሉበት ማበረታታት
በየጊዜዉ ነገሮችን ላያቸዉን ማጽዳጥ። መደበኛ ማጽጃዎች በCOVID-19 ላይ ዉጤታማ ናቸው።
ምክር ለትምህርት ቤቶች
መጋቢት (ማርች) 12 2020 የዋሽንግተን ስቴት ገዢ ጄ እንስሌ በኪንግ፣ ስኖሆሚሽ፣ ና ፒርስ ካውንቲዎች የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመጋቢት 17 እስከ ሚያዚያ 24 ድረስ እንዲዘጉ አሳዉቀዋል። ይህ ዉሳኔ የሆነዉ በከባድ ሁኔታ በቫይረሱ ለተመቱ የዋሽንግተን ካዉንቲዎች የCOVID-19 ስርጭት ምላሽ ነው።
ለሁሉም ሰዉ ምክር
ከርስዎ በተለይ ደግሞ ለCOVID-19 በከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑት ስጋት ለመቀነስ፤
ቤት ይቆዩ በተጨማሪም ሲታመሙ ህዝብ ወዳለበት እንዳይወጡ።
አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ህክምና አካባቢ መሆንን ማስወገድ። ሆኖም ከታመሙ ወደ ዶክተርዎ ቢሮ ከመሄድዎ በፊት ይደዉሉ።
ባይታመሙም እንኳን በተቻለ መጠን ሆስፒታሎችን፣ የረጅም ግዜ መንከባከቢያ ቦታዎችን ወይንም ነርሲንግ ቤቶችን መጎብኘትን ያስወግዱ። ከነዚህ ቦታዎች አንዱ ጋ መሄድ ካለብዎት፣ ከዚያ የሚቆዩበትን ግዜ ይገድቡ በተጨማሪም 6 ጫማ ከታማሚዎች ይራቁ።
አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ድንገተኛ ክፍሎች እንዳይሄዱ። የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቶች ቅድምያ በጣም ለተጎዱት ነዉ ማገለገል ያለባቸዉ። ሳል፣ ትኩሳት ወይንም ሌላ ምልክት ካለብዎ መጀመሪያ መደበኛ ዶክተርዎ ይደዉሉ።
እጅዎን በሳሙናና ዉሃ በየጊዜዉ መታጠብ፣ በሶፍት ወይንም ክንድዎ ላይ ማሰል፣ ና ዐይኖን፣አፍንጫ፣ ወይንም አፎን መንካት ማስወገድን ጭምር ያሉትን ምርጥ የግል ንጽህና ልማዶችን ያድርጉ።
በተለይ ለኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ተጋላጭነት ስጋት ያለብዎት ከሆኑ ከታመሙ ሰዎች ይራቁ።
በየጊዜው የሚነኩ እቃዎችንና ላያቸዉን ያጽዱ (እንደ በር እጀታዎችና መብራት ማብሪያ/ማጥፊያዎች)። መደበኛ የቤት ማጽጃዎች ዉጤታማ ናቸዉ።
ብዙ እረፍት ያግኙ፤ ብዙ ፈሳሽ መጠጣት፤ ጤናማ ምግቦችን መብላት ና ጫናዎትን መቆጣጠር የሰዉነትዎን በሽታ የመከላከል ችሎታን ጠንካራ እንደሆነ ለመጠበቅ።
የ COVID-19 ምልክቶች ወይንም ጥያቄዎች ካለዎት፣ መደወል የሚችሉት፤
የኪንግ ካዉንቲ የኖቬል ኮሮናቫይረስ ጥሪ ማእከል 206-477-3977። ይህ የአገልግሎት መስመር ከጧት 8 ስዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት በየእለቱ ክፍት ነዉ።
የዋሽንግተን ስቴት የኖቬል ኮሮናቫይረስ ጥሪ ማእከል 1-800-525-0127 ና #ን ይጫኑ። ይህ የአገልግሎት መስመር ከጧት 6 ስዓት እስካ ሌሊት 10 ሰዓት በየእለቱ ክፍት ነዉ።
ኦፕሬተሮቹ ከሶስተኛ ወገን አስተርጓሚ ጋር ማገናኘት ይችላሉ። የየትኛው ቋንቋ አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ በእንግሊዘኛ መንገር መቻል አለብዎት። ለረጅም ጊዜ መስመር ላይ ልጠብቁ ይችላሉ።
እርስበርስ ለመረዳዳት ዝግጁ ሁኑ። ጠንካራ የመተሳሰብ ስሜት ከዚህ ከባድ ወቅት እንድናልፍ ይረዳናል።